አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢፈዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሃብት፣ የመስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በህዳሴ ግድብ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።
የቋሚ ኮሚቴው አባላት በዛሬው እለት ጉብኝታቸውም የታላቁ የህዳሴ ግድብ አፈጻጸም ሂደት ተዘዋውረው በመጎብኘት ላይ እንደሚገኙ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
በዚሁ ወቅትም የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ በላቸው ካሳለቋሚ ኮሚቴው ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፥ በዚህም የግድቡ ፕሮጀክት አጠቃላይ አማካይ አፈጻጸም በአሁኑ ወቅት 70 በመቶ መድረሱን አስታውቀዋል።
አያይዘውም ምክትል ስራ አስኪያ በተያዘው ዓመት መጨረሻ ላይ ዩኒት 9 ና 10 ኃይል ለማመንጨት ውሃ የመያዝ ስራ እንደሚከናወን እና በ2013 ዓ.ም ማብቂያ ሁለቱ ዩኒቶች በድምሩ 750 ሜጋ ዋት የሚደርስ ሃይል እንደሚያመነጩ አስገንዝበዋል።