Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለሕብረቱ የመሪዎች ጉባዔ ለሚመጡ እንግዶች የተለየ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 38ኛውን የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ከፍ ባለ ሁኔታ ለማስተናገድ የመዲናችንን ቅድመ ዝግጅት ገምግመናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

የአፍሪካውያንና የዓለም የዲፕሎማቲክ ማዕከል፤ የኅብረ-ብሔራዊነት አርማ የሆነችው አዲስ አበባ ይህን ታሪካዊ ጉባዔ በድምቀት ለማስተናገድ ከወትሮ በተሻለ መልኩ እንግዶቿን ለመቀበል አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገች ነው ብለዋል ከንቲባዋ፡፡

እንግዶችን በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ለመቀበል፣ ነዋሪዎችም ከወዲሁ ከተማችንን ፅዱ በማድረግ ኃላፊነታችንነ በመወጣት የሀገራችንን ስም እና ክብር ከፍ ለማድረግ ተባብረን እንስራ ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Exit mobile version