አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መርጠዋል።
በዚህም 14 ወንድ እና 12 ሴት ለዕጩነት የቀረቡ ሲሆን÷ አትሌት መሰረት ደፋር፣ወ/ሮ ሳራ ሀሰን፣ ወ/ሮ አበባ የሱፍ፣ ኤፍራህ መሀመድ(ዶ/ር)፣ አቶ ቢንያም ምሩፅ፣ አቶ አድማሱ ሳጅን፣ ጌቱ ገረመው(ኢ/ር) እና ትዛዙ ሞሴ(ዶ/ር) የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ሆነው ተመርጠዋል።