አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ 971 ወረዳዎች በሀገራዊ ምክክሩ ተደራሽ መደረጋቸውን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ የኦሮሚያ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብ ሒደት አካል የሆነውን የተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ምክክር እያካሄደ ነው።
በመድረኩ በክልሉ የሚገኙ በርካታ የማህበረሰብ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ተገኝተዋል።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ስላሴ በዚህ ወቅት÷ሀገራዊ የምክክር ኮማሽኑ ህብረተሰቡ አጀንዳዎቹን በሚገባ ማቅረብ እንዲችል በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም በሀገር አቀፍ ደረጃ 971ወረዳዎች በሀገራዊ ምክክሩ ተደራሽ ማድረጉን ነው የተናገሩት፡፡
1 ሺሕ 700 ባለድርሻ አካላት የሚገኙበት ሁለተኛው ምዕራፍ የኦሮሚያ ክልል የምክክር ሂደትም ነገ በአዳማ ከተማ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።
በአሸናፊ ሽብሩ