አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ወደ ካምፕ የገቡ የኦነግ ታጣቂዎች ስልጠና ጀመሩ።
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት መረጃ እንዳመለከተው፤ ታጣቂዎቹ በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ አዋሽ ቢሾላ ፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም ነው ስልጠና የጀመሩት።
በክልሉ መንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት በመተግበር ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ተገልጿል።