Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በ28 ሚሊየን ብር የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች ተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በሱማሌ ክልል ደጋሃቡር ከተማ በ28 ሚሊየን ብር የገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች አስረክቧል፡፡

በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ተገኝተዋል፡፡

ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት የተጀመረው ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች ቤት የመገንባት መርሐ ግብር መንግስት ለሰብዓዊ ልማት የሰጠውን ትኩረት ያሳያል፡፡

ሚኒስቴሩ ዛሬ ለነዋሪዎች ያስረከባቸውን ጨምሮ እስካሁን 97 መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ማስተላለፉንም በማህበራዊ ትስስር ገጸቸው አስፍረዋል፡፡

Exit mobile version