የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እቃ ጫኝ አውሮፕላን በሻንጋይ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ እቃ በሚጭነበት ወቅት በእሳት ተያያዘ

By Tibebu Kebede

July 22, 2020

ሁሉም የአውሮፕላኑ ሰራተኞ በመልካም ደህንነት ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።

አየር መንገዱ አደጋውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ቦይንግ 777 ኢቲ ኤአርኤች እቃ ጫኝ አውሮፕላን እቃ ሲጭን በነበረበት ወቅት በእሳት መያያዙን ገልጿል።

አውሮፕላኑ ከሻንጋይ ወደ ሳኦ ፓሎ መደበኛ የካርጎ በረራ ለማድረግ ዝግጅት ላይ የነበረ መሆኑ ነው የተነገረው። በአውሮፕላኑ ላይ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠርም ከሚመለከታቸው ሁሉም አካላት ጋር ኢትዮጵያ በትብብር መስራቷን አየር መንገዱ አስታውቋል።

የእሳት አደጋው ምክንያትም በሚመለከታቸው አካላት እየተጣራ እንደሚገኝ ተነግሯል።