Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቱኒዚያ በጀልባ መገልበጥ አደጋ የ7 ሰዎች ህይዎት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቱኒዚያ ምሥራቃዊ የባሕር ጠረፍ በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ የሠባት ሰዎች ህይዎት ሲያልፍ ስድስት ሰዎች የገቡበት አለመታወቁ ተገለጸ፡፡

የቱኒዚያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ወደ ጣሊያን የባህር ጠረፍ በማምራት ላይ በነበረ የጀልባ አደጋ የሠባት ስደተኞችን አስከሬን ማግኘታቸውንና 27 ሰዎችን ማዳን መቻላቸው ተሰምቷል፡፡

ሆኖም በአንጻሩ ሥድስት ሰዎች የገቡበት እንዳልታወቀና ፍለጋው አሁንም መቀጠሉም ነው የተነገረው፡፡

የቱኒዚያ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር፥ ከሰሀራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ ምሽት በሀገሪቱ ምስራቃዊ የባህር ጠረፍ አካባቢ መገልበጧን በሰጠው መግለጫ ጠቁሟል፡፡

በአጠቃላይ በጀልባው 42 ሰዎች እንደነበሩ የተገለጸ ሲሆን ፥ የሜዲትራኒያን ባህር ወደ አውሮፓ ለሚጓዙ ስደተኞች በዓለም ላይ ካሉት አደገኛው እንደሆነ ይነገራል፡፡

የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) የቅርብ ጊዜ መረጃ በዚህ ዓመት በሜዲትራኒያን ባህር የ2 ሺህ 50 ሰዎች ህይዎት ማለፉን እንደሚያመላክት የዘገበው የኳታር ኒውስ ኤጀንሲ ነው።

Exit mobile version