Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

2ኛው ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን የሚሰጠውን ምቹ አገልግሎት እንደሚያጠናክር ተመላከተ

አዲስ አበባ ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ 2ኛው ኤርባስ ኤ350-1000 (ET-BAX) አውሮፕላን አየር መንገዱ ለምቹ እና ዘመናዊ የደንበኞች አገልግሎት እየሰጠ ያለውን ትኩረት እንደሚያጠናክር ተገለጸ፡፡

ከዚህ ባለፈም አየር መንገዱ በአቪዬሽን ዘርፍ የአፍሪካ መሪ አየር መንገድ መሆኑን እንደሚያሳይ ነው የተጠቆመው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለተኛውን ኤርባስ A350-1000 (ET-BAX) በቅርቡ ወደ ሀገር ማስገባቱን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡

የአየር መንገዱ ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ መግባቱ ይታወሳል።

 

Exit mobile version