አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ5 ሺህ 56 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርግ 304 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በቫይረሱ የተገኘባቸው ከአዲስ አበባ ከተማ 157፣ ከትግራይ ክልል 36፣ ከኦሮሚያ ክልል 46፣ ከጋምቤላ ክልል 26፣ ከአማራ ክልል 12፣ ከአፋር ክልል 17፣ ከሶማሌ ክልል 7፣ ከሐረሪ ክልል 2 እና ከደቡብ 1 ናቸው፡፡
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ለ336 ሺህ 322 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 10 ሺህ 511 ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ባለፉት 24 ሰአታት የ3 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 173 ደርሷል፡፡
56 የኮሮና ቫይረስ ታካሚዎች ደግሞ በፅኑ ህክምና መከታታያ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡ም ነው ያለው፡
በተያያዘም 153 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን ይህን ተከትሎም 5 ሺህ 290 ሰዎች በአጠቃላይ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡