የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ታዬ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ

By ዮሐንስ ደርበው

December 04, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የ12 ሀገራትን አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል።

በዚሁ መሠረት በኢትዮጵያ የቬንዝዌላ፣ አልጄሪያ፣ ፈረንሳይ፣ የአውሮፓ ሕብረት፣ አርጀንቲና፣ ጀርመን፣ ናሚቢያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ስሎቬኒያ፣ ግሪክ፣ ኮሎምቢያ እና ሉግዘምበርግ አምባሳደሮችን ጨምሮ የሌሎችንም ሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ፕሬዚዳንቱ በትናንትናው ዕለት የበርካታ ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ መቀበላቸው ይታወሳል፡፡