Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአፋርና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በነበረው ግጭት የተያዙ እስረኞች ልውውጥ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር እና ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረውን ግጭት ለመፍታት የተጀመረውን የሰላም ስምምነት አስመልክቶ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በክልሎቹ አዋሳኝ አካባቢዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት ተይዘው የነበሩ አካላት እንዲቀላቀሉ በማድረግ በቆየው ስምምነት መሠረት የእስረኞች ልውውጥ መካሄዱን የሰላም ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

የእስረኛ ልውውጥ የተደረገው የሰላም ሚኒስቴር ከሁለቱ ክልሎች፣ ከፌደራል ፖሊስ እና መከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን ተቀናጅቶ ባካሄደው ተከታታይ ውይይት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በአካባቢው የነበረውን አለመግባባት በውይይት በመፍታት ሰላምን ለማምጣት ብሎም ዳግም ወደ ግጭት የሚያመሩ ጉዳዮች ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ ውይይቶች እንዲደረጉ በር ይከፍታል ተብሏል፡፡

Exit mobile version