የሀገር ውስጥ ዜና

ኮሚሽኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አጀንዳዎችን ተረከበ

By ዮሐንስ ደርበው

December 04, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሰባት ክፍሎችና በ64 ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ያዘጋጃቸውን አጀንዳዎች መረከቡን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

አጀንዳዎቹን የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ከሌሎች ኮሚሽነሮች ጋር በጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ ከተመራው የምክር ቤቱ የሥራ አስፈፃሚ አባላት ቡድን መረከባቸው ተገልጿል፡፡

መሥፍን  (ፕ/ር) በዚሁ ወቅት ኮሚሽኑ ከምክር ቤቱ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሞ በጋራ እየሠራ መቆቱን አውስተው÷ ኮሚሽኑ በተቋማትና በማህበረሰብ ክፍሎች ተደራጅተው የሚቀርቡ አጀንዳዎችን በአግባቡ እንደሚጠቀምባቸው አስታውቀዋል፡፡

ሌሎች ተቋማትና ማህበራትም የተደራጁ አጀንዳዎቻቸውን እንዲያስረክቡ ጥሪ ማቅረባቸውን የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

አቶ ሰለሞን በበኩላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች አካታች ሀገራዊ ምክክር እንዲደረግ ሚናቸውን መወጣት እንደሚገባቸው አስገንዝበው÷ ዛሬ ለኮሚሽኑ ያስረከብናቸው አጀንዳዎች በምክርቤቱ በሙሉ ድምፅ የፀደቁ ናቸው ብለዋል፡፡