Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለቀድሞ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር  ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)የሰላም ሚኒስትር ሆነው ለተሾሙት የቀድሞ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እድሪስ  ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

 

አቶ መሐመድ እድሪስ ባለሥልጣኑን በዋና ዳይሬክተርነት በመሩበት ወቅት ተቋሙ በተለያዩ ዘርፎች ለውጦችን እንዲያስመዘግብ መስራታቸው ተገልጿል።

 

ተቋሙ ያስመዘገበው ለውጥ የሁሉም የጋራ ስራ መሆኑን የገለፁት አቶ መሐመድ በቀጣይም ከባለሥልጣን መስሪያቤቱ ጋር በትብብር እንደሚሰሩ መናገራቸውን የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

አቶ መሐመድ ከሶስት ዓመታት በላይ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲመሩ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

 

Exit mobile version