አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል።
ፕሬዚዳንት ታዬ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የሜክሲኮ አምባሳደር አሊሃንድሮ ኤስቲቪል ካስትሮ፣ የሱዳን አምባሳደር ኤልዚኢን ኢብራሂም ሃሰን፣ የኒኳራጓይ አምባሳደር አሊ ጋርዝ፣ የኢራን አምባሳደር አሊ ሪዛኢ፣ የጋቦን አምባሳደር ሊሊ ስቴላ እና የቤልጄም አምባሳደር አኒል ቨርስቲቺል የሹመት ደብዳቤን ነው የተቀበሉት።
በበተመሳሳይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኢትዮጵያ የተሾሙ የቻይና፣ ጋና፣ ዴንማርክ፣ አየርላንድ፣ እስራኤልና ኔዘርላንድ አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል።
አምባሳደሮቹ በኢትዮጵያ ሀገራቸውን ወክለው በመሾማቸው ደስተኛ መሆናቸውን በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
የሀገራቱ አምባሳደሮች በቆይታቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን የምጣኔ ሀብት፣ ፖለቲካና ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰሩም ተናግረዋል።