አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከስታዲየም ውጭ የዓመቱ ምርጥ የጎዳና ላይ ውድድር አትሌት ሽልማትን ላሸነፉ ኢትዮጵያዊ አትሌቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
አትሌት ታምራት ቶላ እና አትሌት ሲምቦ አለማየሁ የዓመቱ ምርጥ የጎዳና ላይ ውድድር አትሌት ሽልማትን ማሸነፋቸው ይታወቃል፡፡
አትሌት ታምራት ቶላ ከስታዲየም ውጭ የዓመቱ ምርጥ የጎዳና ላይ ውድድር አትሌት ሽልማትን ያሸነፈ ሲሆን÷ሌላኛዋ አትሌት ሲምቦ አለማየሁ ደግሞ የዓመቱ ምርጥ ታዳጊ አትሌት ሽልማትን አሸንፋለች።
ፕሬዚዳንት ታዬ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ አትሌት ታምራት ቶላና አትሌት ሲምቦ አለማየሁ የጅግኖች አትሌቶችን ፈለግ በመከተል ድል ማስመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡
አትሌቶቹ በዘርፉ ያስመዘገቡት ስኬት ለቀጣይ ተተኪ አትሌቶች ተስፋ የሚሰጥ ነው ሲሉም አውስተዋል፡፡