Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሐረሪ ክልል ከጥቅምት ወር ጀምሮ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ በአዲሱ ጭማሬ እንዲከፈል ተወሰነ

 

አዲስ አበባ፣ 23 ሕዳር፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ከጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ጀምሮ የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ሕግን በተከተለ አግባብ ተግባራዊ እንዲደረግ ውሳኔ አሳለፈ።

ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ባካሄደው ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎቸ ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በዚህም በመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ የውሳኔ ሀሳብ እና የመንግስት መስሪያ ቤቶች የአገልግሎት ክፍያ ተመንን ለማሻሻል በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ባሳለፈው ውሳኔ፤ ካለፈው የጥቅምት ወር ጀምሮ የመንግሥት ሠራተኛ የደመወዝ ጭማሪ ህግን በተከተለ አግባብ ተግባራዊ እንዲደረግ ውሳኔ ማሳለፉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የመስተዳድር ምክር ቤቱ በመቀጠል የመንግስት መስሪያ ቤቶች የአገልግሎት ክፍያ ተመንን ለማሻሻል በቀረበ የመስተዳድረ ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ ላይ የተወያየ ሲሆን÷ ደንቡ ከመስተዳድር ምክር ቤቱ አባላት የተሰጡ አስተያየቶችን አካቶ ስራ ላይ እንዲውል ውሳኔ አሳልፏል።

Exit mobile version