ስፓርት

በጊኒ የእግር ኳስ ዳኛ ውሳኔን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት የ56 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Meseret Awoke

December 02, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በጊኒ የእግር ኳስ ዳኝነት ላይ የተላለፈን ውሳኔ ተከትሎ በተፈጠረ ግጭትና መረጋገጥ የ56 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

በጊኒ ንዜርኮሬ ከተማ በተደረገ የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ላቤ የተሰኘ የእግር ኳስ ክለብ ላይ የተላለፈ የዳኝነት ውሳኔን ተከትሎ ደጋፊዎች ድንጋይ መወርወር መጀመራቸው ተመላክቷል፡፡

ግጭቱን ለመቆጣጠርም ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ የተጠቀመ ሲሆን ፥ ተቃዋሚዎቹ የንዘሬኮሬ ፖሊስ ጣቢያን በእሳት ማያያዛቸው ተገልጿል፡፡

ድርጊቱን ተከትሎ የተፈጠረው ግጭትና መረጋገጥም ለብዙዎች ሕልፈት ምክንያት መሆኑ ነው የተጠቆመው፡፡

የጊኒው ጠቅላይ ሚኒስትር ባህ ኦሪ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የተፈጠረውን ክስተት አውግዘው ፤ መንግስት ሁሉንም መረጃ ካጠናቀቀ በኋላ ይፋ እንደሚያደርግ መናገራቸውን የዘገበው አልጀዚራ ነው፡፡