አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ ለዩክሬን ተጨማሪ ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡
በኬቭ ጉብኝት ላይ የሚገኙት ቻንስለሩ፤ ጀርመን ለዩክሬን ጠንካራ ወታደራዊ ድጋፍ በማድረግ ከአውሮፓ ሀገራት ቀዳሚ ሆና ትቀጥላለች ብለዋል፡፡
በተያዘው የፈረንጆቹ የታህሰስ ወር ብቻ 650 ሚሊየን ዩሮ የሚገመት የወታደራዊ ቁሳቁስ ድጋፍ ለዩክሬን እንደሚላክ አረጋግጠዋል።
የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ለሁለተኛ ጊዜ በኬቭ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ቻንስለሩ፤ ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅትን (ኔቶ) እንድትቀላቀል ጫና መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘሌንስኪ ጋር እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡
በጀርመን ዳግም ለመመረጥ ፍላጎት ያላቸው ቻንስለሩ፤ ለዩክሬን የፈቀዱት ድጋፍ ጦርነቱን በማይደግፉ ጀርመናውያን ዘንድ ድምጽ ሊያሳጣቸው መነገሩን ግሎባል ዩሮፕ ዘግቧል፡፡