የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ በሥርዓተ-ምግብ ላይ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

By ዮሐንስ ደርበው

December 02, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በሥርዓተ-ምግብ ማጠናከሪያ ተግባራት በይበልጥ ውጤታማ ለመሆን በምታደርገው ጥረት ኖርዌይ ድጋፏን እንምታጠናክር አስታወቀች፡፡

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ከኖርዌይ አምባሳደር ስቲያን ክሪስተንሰን ጋር ካርቦን ሽያጭን ጨምሮ በትብብር በሚሠሩ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

የተራቆቱ አካባቢዎች በተፋሰስ ልማትና አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በደን በመሸፈናቸው የካርቦን ሽያጭን ጨምሮ ዘርፈ-ብዙ ጥቅሞች መገኘታቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚህም በየክልሎቹ የተደራጁ የደን ማኅበራት የካርቦን ሽያጭ በማድረግ ተጨማሪ ገቢ እያገኙ ነው ብሏል፡፡

በዛሬው ውይይትም በክልሎች ያለውን የካርቦን ሽያጭ ተሞክሮ ሀገራዊ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ እና በጋራ በሚሠሩባቸው ጉዳዮች ላይ በመምከር መግባባት ተደርሷል፡፡

በተጨማሪም በሥርዓተ-ምግብ ማጠናከሪያ ተግባራት ላይ የተወያዩ ሲሆን÷ በዚህም ኢትዮጵያ በይበልጥ ውጤታማ እንድትሆን ወደፊት በጋራ ለመሥራት መስማማታቸው ተገልጿል፡፡