አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተጻፈ ደብደዳቤ አስመስሎ በማዘጋጀት ወደ ውጪ ሀገራት ለስራ እድል እንልካለን በሚል ግለሰቦች ዜጎችን እያታለሉ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጸው÷ የሚኒስቴሩን አርማ እና ማህተም በማስመሰል ሀሰተኛ ደብዳቤዎች ተዘጋጅተዋል።
በዚህም ከሚኒስቴሩ ዕውቅና እንደተሰጣቸው በማስመሰል ዜጎችን በማጭበርበር ድርጊት መሰማራታቸውን እንደደረሰሰበት በመግለጽ፤ ህብረተሰቡ ግለሰቦቹ የማጭበርበር ድርጊት እየፈጸሙ እንደሆነ በመገንዘብ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት አስገንዝቧል።
በዚህ መንገድ በሚዘጋጁ ሀሰተኛ ደብዳቤዎችም በርካታ ዜጎች እየተታለሉ መሆኑንም አስገንዝቧል፡፡
ስለሆነም ዜጎች መሰል መረጃዎችን ከሚመለከተው አካል በማረጋገጥ ከአላስፈላጊ ጥፋት ራሳቸውን እዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የድርጊቱን ፈጻሚዎች በህግ ተጠያቂ ለማድረግም አስፈላጊው ክትትል እየተደረገ እንደሆነ ተገልጿል።