አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ታምራት ቶላ ከስታዲየም ውጭ የዓመቱ ምርጥ የጎዳና ላይ ውድድር አትሌት ሽልማትን አሸንፏል፡፡
አትሌት ታምራት ቶላ በፓሪስ ኦሎምፒከ አዲስ ክብረ ወሰን በማሻሻል በማሸነፍ ለሀገሩ ብቸኛውን ወርቅ ሜዳሊያ ማስገኘቱ ይታወሳል።
ሌላኛዋ አትሌት ሲምቦ አለማየሁ ደግሞ የዓመቱ ምርጥ ታዳጊ አትሌት ሽልማትን ማሸነፏን የዓለም አትሌቲክስ መረጃ አመልክቷል።
አትሌት ሲምቦ አለማየሁ በፔሩ ሊማ ከ20 ዓመት በታች በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ክብረ ወሰን በማሻሻል እንዲሁም፤ በቡዳፔስት በተደረገው የዓለም ሻምፒዮና እና በፓሪሱ ኦሎምፒክ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሀገሯን ወክላ ውጤት አስመዝግባለች።
የሴቶች የዓመቱ የጎዳና ላይ ውድድር ምርት አትሌት ሽልማትን ደግሞ ለኔዘርላንድስ የምትሮጠው አትሌት ሲፋን ሀሰን አሸንፋለች፡፡