ስፓርት

ቼልሲ እና ማንቼስተር ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

By Mikias Ayele

December 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ቼልሲ እና ማንቼስተር ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

ቀን 10 ሰዓት ከ30 በስታምፎርድ ብሪጅ አስቶንቪላን ያስተናገደው ቼልሲ በኒኮላስ ጃክሰን ፣ ኤንዞ ፈርናንዴዜ  እና ኮል ፓልመር  ጎሎች 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ሌላ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ ኤቨርተንን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ሲያሸንፍ ፣ጆሽዋ ዚርኬዜ(ሁለት) እና ማርከስ ራሽፎርድ(ሁለት) ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡

ማንቼስተር ዩናይትድ ብልጫ በወሰደበት ጨዋታ ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የመጀመሪያ የፕሪሚየርሊጉ ድላቸውን አስመዝግበዋል፡፡

በለንደን ስታዲየም በተደረገ ሌላ ጨዋታ ደግሞ ቶተንሃም እና ፉልሃም አንድ አቻ ሲለያዩ ቤርናን ጆንሰን ለቶተንሃም ቶማስ ካርኔይ ደግሞ የፉልሃምን ጎል አስቆጥረዋል፡፡

የ13ኛ ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብሮች ሲቀጥሉ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ሊቨርፑል ከማንቼስተር ሲቲ በአንፊልድ የመሚያደርጉት የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ይጠበቃል፡፡