ስፓርት

በቫሌንሺያ ማራቶን አትሌት መገርቱ ዓለሙ አሸነፈች

By Meseret Awoke

December 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ረፋድ ላይ በተካሄደው የቫሌንሺያ ሴቶች ማራቶን ውድድር አትሌት መገርቱ ዓለሙ አሸናፊ ሆናለች።

አትሌቷ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 2 ሠዓት ከ16 ደቂቃ ከ49 ሰከንድ ወስዶባታል፡፡

እንዲሁም አትሌት ጥሩዬ መስፍን ሦስተኛ ደረጃን ስትይዝ፥ ዑጋንዳዊቷ ስቴላ ቼሳንድ ሁለተኛ ሆና አጠናቅቃለች፡፡