ስፓርት

በቫሌንሺያ ማራቶን አትሌት ደረሳ ገለታ 2ኛ ደረጃን ያዘ

By Meseret Awoke

December 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በስፔን ቫሌንሺያ በተካሄደው የወንዶች ማራቶን ውድድር አትሌት ደረሳ ገለታ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቀቀ፡፡

ኬንያውዩ አትሌት ሴባስቲያን ሳዌ ውድድሩን በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ÷ ሌላኛው ኬንያውይ አትሌት ዳኒኤል ማቴኮ ሦስተኛ ሆኗል፡፡

እንዲሁም አትሌት ጪምዴሳ ደበሌ 6ኛ እና የአምናው የውድድሩ አሸናፊ አትሌት ሲሳይ ለማ 10ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል፡፡

በዘንድሮው ውድድር ላይ የሦስት ጊዜ ኦሊምፒክ ባለ ድሉ አትሌት ቀነኒሳ በቀለም ተሳተፏል፡፡