በትግራይ ክልል የግሪሳ ወፍን ለመከላከል የኬሚካል ርጭት ተከናወነ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የተከሰተውን የግሪሳ ወፍ መንጋ ለመከላከል በአውሮፕላን የተደገፈ የኬሚካል ርጭት ተከናወነ።
የግሪሳ ወፍ መንጋን ከመከላከል ጎን ለጎንም የምርት መሰብሰብ ሥራ በቅንጅት እየተከናወነ መሆኑን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡