ስፓርት

በወዳጅነት ዐደባባይ ከ10 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

By ዮሐንስ ደርበው

December 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሚከበረውን የፀረ-ሙስና ቀን ምክንያት በማድረግ በወዳጅነት ዐደባባይ ከሁሉም የመዲናዋ ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ ከ10 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሂዷል፡፡

የአካል ብቃት እንቅስቃሴው የተካሄደው÷ “ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል የነገን ስብዕና ይገነባል” በሚል መሪ ሐሳብ ነው፡፡

በዚሁ ወቅትም ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ወጣቶች የማይተካ ሚና ስላላቸው በፀረ-ሙስና ትግሉ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ወጣቶች የእርስ በርስ ትስስራቸውን በማጠናከር ሰርቶ የመለወጥ ባህልን ሊያዳብሩ እንደሚገባም ተገልጿል፡፡