Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሀገር ውስጥ የመድሃኒት ምርትን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)የሀገር ውስጥ የመድሃኒት ምርትን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክ ከተመራ ልዑክ ጋር በጤናው ዘርፍ በትብብር በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት÷ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ ጋር በጤናዉ ዘርፍ ለረጅም ግዜ በትብብር እየሰራች መሆኑን ገልጸው የፈረንሳይ ህዝብ እና መንግስት ለኢትዮጵያ እያደረጉት ስላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በሽታ መከላከል፣ የእናቶች እና ህጻናት ጤና፣ የቤተሰብ እቅድ እና ስነ-ተዋልዶ ጤና እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ስልጠና ጤና ሚኒስቴር ከፈረንሳይ የልማት አጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር መስራት የሚፈልግባቸው የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክ በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት እያደገ መምጣቱን ገልጸው፤ በተለይም በጋራ በመሆን የኢትዮጵያን የሀገር ውስጥ የመድሃኒት ምርትን ማሳደግ በሚቻልበት ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version