Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከ100 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባቸውን ፕሮጀክቶች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከ100 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባቸውን የተለያዩ ፕሮጀክቶች አስመርቋል፡፡

89ኛ የምስረታ በዓሉን እያከበረ የሚገኘው የአየር ኃይሉ፤ የሰራዊቱን ኑሮ ለማሻሻል እና የውጊያ መሠረተ ልማቶችን ለማሟላት ታሰቢ በማድረግ ዘመናዊ የአብራሪዎች መኖሪያ ቤት፣ መመገቢያ አዳራሽ፣ የሠራዊት አባላት መኖሪያ ቤትና የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድን ጨምሮ ሌሎች የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን አከናውኗል።

ለፕሮጀክቶቹ ግንባታ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ መደረጉም ተገልጿል።

ተቋሙ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን ያስገነቧቸው ፕሮጀክቶች የሠራዊቱን ችግር የሚቀርፉና ተቋሙ ዘመናዊ ሰራዊት ለመገንባት የሚያደርገውን ጥረትም የሚያግዙ መሆናቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ግዳጁን በብቃት የሚወጣ ደስተኛ አሀድና ሠራዊት ለመገንባት ምቹ የሥራ እና የመኖሪያ አካባቢን መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ በቀጣይም አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በመንደፍና የጀመራቸውን ፕሮጀክቶች በማጠናቀቅ ለታላቅ ሀገር የሚመጥን አየር ኃይል ለመገንባት የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት እንደሚሰራ ተጠቁሟል፡፡

Exit mobile version