በአዲስ አበባ የባቡር ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
በዚሁ መሠረት ከታኅሣስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በመዲናዋ ተግባራዊ የሚደረግ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ታሪፍ አሁን እየተሰጠበት ካለው 10 ብር ወደ 20 ብር ማሻሻያ መደረጉን ቢሮው አስታውቋል፡፡
የታሪፍ ማሻሻያው ከታኅሣስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ታውቆ ተፈፃሚ እንዲደረግም ቢሮው አሳስቧል፡፡
ድርጅቱ ከሰሜን ወደ ደቡብ (ከጊዮርጊስ – ቃሊቲ) እና ከምስራቅ ወደ ምዕራብ (ከአያት – ጦር ኃይሎች) የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት በየቀኑ በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ መንገደኞችን እንደሚጓጉዝ ተገልጿል፡፡