የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ የሁለት ቀን የኤርትራ ጉብኝታቸውን  አጠናቀው አዲስ አበባ ተመለሱ

By Meseret Demissu

July 19, 2020

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 12 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ እና ልኡካቸው የሁለት ቀን ይፋዊ የኤርትራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ሐምሌ 12 ቀን 2012 ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ጉብኝቱ የኢትዮጵያንና የኤርትራ የሰላም ስምምነት አዲስ ምዕራፍ ከተደረሰ እና የሀገራቱ መልካም ጉርብትናና የዲፕሎማሲያዊ የግንኙነት ከተበሰረ ሁለት ዓመት በኋላ የተካሄደ ነው፡፡

ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ እና በቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡ እንዲሁም የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችንም ጎብኝተዋል፡፡