አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ኒውዮርክ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ከአራት ወደ ሰባት ማሳደጉን አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ ከሕዳር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከአዲስ አበባ ወደ ኒውዮርክ በሳምንት አራት ጊዜ ሲያደርግ የነበረውን በረራ ነው ወደ ሰባት ያሳደገው፡፡
በዚህ መሰረትም ከፊታችን እሑድ ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኒውዮርክ ከተማ ዕለታዊ በረራ እንደሚጀምር ተመላክቷል፡፡