Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ካናዳ በጤናው ዘርፍ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ እንደምታጠናክር ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር ጆሿ ታባህ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ሁለቱ ሀገራት በጤናው ዘርፍ በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ዶ/ር መቅደስ÷በኢትዮጵያና ካናዳ መካከል ያለው ወዳጅነት የቆየ መሆኑን ጠቁመው÷ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር በትኩረት ከሚሰራባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ውስጥ አንዱ የጤና ባለሙያዎች የሥራ ፈጠራና የማበረታቻ ጥቅል መሆኑን አንስተዋል፡፡

በዚህ ዙሪያም ከውጪ ሀገራትና አጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

አምባሳደር ጆሿ ታባህ በበኩላቸው÷የኢትዮጵያን የጤና ስርዓት ለማጠናከር ካናዳ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

Exit mobile version