አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አቶ መሐመድ እድሪስን የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር በማድረግ ሾመዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አቶ መሐመድ እድሪስን የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር በማድረግ መሾማቸውን አስታውቋል።
አቶ መሐመድ እድሪስ ከመጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በመሆን ሲያገለግሉ እንደነበር ይታወቃል።