ቢዝነስ

በቻይና ዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ዐውደ-ርዕይ ላይ የኢትዮጵያ ምርቶች እየተዋወቁ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

November 29, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤጂንግ እየተካሄደ በሚገኘው የቻይና ዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ዐውደ-ርዕይ ላይ የኢትዮጵያ ምርቶች እየተዋወቁ ነው፡፡

በዐውደ-ርዕዩ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ አምራቾች፣ አስመጪዎች፣ ላኪዎች እና አቅራቢዎችም እየተሳተፉ ነው፡፡

ከዐውደ-ርዕዩ ጎን ለጎንም የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት፣ የንግድና የቱሪዝም ዕድሎች የሚያስተዋውቅ መድረክ ተካሂዷል።

አምባሳደር ደዋኖ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በኢትዮጵያ እና ቻይና መካከል ያለው ሁለንተናዊ የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን አስረድተዋል፡፡

በሀገራቱ መካከል እየተካሄደ ያለው የኢንቨስትመንት እና ንግድ ልውውጥም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ነው የገለጹት፡፡

ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ማድረጓን ያስታወሱት አምባሳደሩ÷ የማሻሻያ ሥራው ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ በመሆኑ የቻይና ባለሀብቶች የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

በአፈወርቅ እያዩ