የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) የአውሮፓ እና የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን በጽህፈት ቤታቸው ተቀበሉ

By Feven Bishaw

November 29, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአውሮፓ እና የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ጂያን-ኖኤል ባሮትን በጽህፈት ቤታቸው ተቀበሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ “ዛሬ ጠዋት የአውሮፓ እና የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ጂያን-ኖኤል ባሮትን በሁለቱ ሀገሮቻችን ባሉ ትስስሮች ላይ ለመነጋገር በጽህፈት ቤታችን ተቀብያለሁ” ብለዋል።