የሀገር ውስጥ ዜና

የአየር ኃይል የምስረታ በዓል አከባበር ማጠቃለያ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው

By amele Demisew

November 29, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል 89ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አከባበር የማጠቃለያ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው፡፡

የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ የሠራዊቱ አመራሮች እና የተለያዩ ሀገራት የመከላከያ አታሼዎች በመርሐ-ግብሩ ላይ ተገኝተዋል፡፡

በአየር ኃይሉ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች የተመረቁ ሲሆን÷ ከነዚህም መካከል የአብራሪዎች መኖሪያ ቤት፣ የሠራዊቱ መመገቢያ አዳራሽ እና የአስፓልት መንገድ ይገኙበታል፡፡

እንዲሁም የመከላከያ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽኖች እና የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ያዘጋጁት ዐውደ-ርዕይ ተከፍቷል።

በዐውደ-ርዕዩ  ላይም የአየር ኃይሉን አሁናዊ አቅም የሚያሳዩ የተለያዩ የአቪዬሺን እና ልዩ ልዩ ወታደራዊ ትጥቆች ለዕይታ ቀርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ትናንት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ይፋ ያደረጓት በአየር ኃይሉ የተሠራች ፀሐይ 2 የተሰኘች አውሮፕላንን ጨምሮ ድሮንና ሌሎች ወታደራዊ ትጥቆችም በዐውደ-ርዕዩ ቀርበዋል።

በታሪኩ ለገሰ