አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 39ኛው የጉሚ በለል የውይይት መድረክ “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ውይይቱ በ19ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በመድረኩ የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ እሸቱ ስርኔሳ፣ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ሕዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ በአርባምንጭ ከተማ እንደሚከበር ይታወቃል፡፡
በአመርቲ ተስፋዬ