ሩሲያና ቻይና በጃፓን ባሕር የጋራ የአየር ላይ ቅኝት አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያና ቻይና በጃፓን ባሕር የጋራ የአየር ላይ ቅኝት ማድረጋቸውን የቻይና መካላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች የተደረገው የጋራ የአየር ላይ ቅኝቱ የሀገራቱ ዓመታዊ የትብብር እቅድ ማዕቀፍ አካል መሆኑ ተገልጿል፡፡
ሩሲያና ቻይና በጃፓን ባሕር መሰል የጋራ የአየር ላይ ቅኝት ሲያደርጉ ከፈርንጆቹ 2019 ወዲህ ይህ 9ኛ ጊዜያቸው ነው ተብሏል፡፡
የአየር ላይ ቅኝቱ የሀገራቱን ስትራቴጂያዊ ትብብር ማጠናከር እና የቀጣናውን ሰላም ለማስፈን ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ሩሲያና ቻይና ባሳለፍነው ሐምሌ ወር በሰሜን ፓስፊክ በአሜሪካዋ አላስካ ግዛት አቅራቢያ የኒውክሌር አቅም ባላቸው ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች የጋራ የአየር ላይ ቅኝት ማድረጋቸውን ሬውተርስ በዘገባው አስታውሷል፡፡