አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በዓሣ ምርት የተሠማሩ 22 ማኅበራት ካለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ 561 ነጥብ 5 ቶን የዓሣ ምርት ለአካባቢው እና ማዕከላዊ ገበያ አቀረቡ፡፡
ግድቡ ከኃይል ማመንጨት ባለፈ ለወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ የእንስሳት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ብርሃኑ ኢተቻ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
በዓሣ ማምረት ለተሠማሩ ማኅበራትም የማምረቻ ቁሳቁሶችን ጨምሮ የገበያ ትስስር እየተፈጠረላቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በሰለሞን ይታየው