አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)የጥራት መንደር የኢትዮጵያን ተወዳዳሪነት በጉልህ የሚያሳድግ መሆኑን መንደሩን የጎበኙ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ገለጹ።
የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ አመት የምስረታ በአል “የሀሳብ ልእልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ መሆኑ ይታወቃል።
የዚህ አካል የሆነ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
በዚህም ጎብኝዎች በቅርቡ ወደ ስራ የገባውን ጥራት መንደር የጎበኙ ሲሆን÷ ጎብኝዎች ተቋሙ ኢትዮጵያ ጥራት ያለው ምርትን ወደ ውጭ በመላክ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችላት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በዚህ ደረጃ መገንባቱም መንግስት ለጥራት የሰጠው ትኩረት ከፍተኛ መሆኑን የሚያሳይ መሆኑን ገልጸው መንግስት አሁንም ለጥራት የሰጠውን ትኩረት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመላክተዋል።
ጥራት ለየትኛውም ጉዳይ ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ጎብኝዎቹ “ሁሌም ጥራት የስራችን ማእከል መሆን አለበት” ማለታቸውን ከብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ባለፈው ሳምንት የጥራት መንደርን መርቀው ስራ ማስጀመራቸው ይታወሳል።