የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያና ኩዌት የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ስምምነት ላይ ውይይት ተካሄደ

By Melaku Gedif

November 28, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሰኢድ ሙሁመድ (ዶ/ር) ከሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንጽላ የአፍሪካና ዓለም አቀፍ ሕግ ጉዳዮች ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያና ኩዌት መካከል የተፈረመውን የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ስምምነት በፍጥነት መተግበር በሚቻልባቸው ሁኔታዎችና ቴክኒካል ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በቀጣይ በአጭር ጊዜ ውስጥ በመገናኘት ቀሪ ጉዳዮች ላይ ለመወያትት ከስምምነት መድረሳቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡