Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው እየሰሩ ያሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ቁጥር 5 ሺህ 200 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው እየሰሩ ያሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ቁጥር 5 ሺህ 200 መድረሱን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ገለጸ።

ከህዳር 27 እስከ 29 ቀን 2017 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበረውን 4ኛውን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት በማስመልከት ባለስልጣኑ መግለጫ ሰጥቷል።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፋሲካው ሞላ በመግለጫቸው ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በርካታ የሪፎርም ስራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል።

ከዚህ ቀደም ለስራ አዳጋች የነበሩ ህጎች እና ደንቦችን ከመቀየር ጀምሮ በርካታ ለውጦች መደረጋቸውን ጠቅሰው÷ አሁን ላይ የዴሞክራሲ ምህዳሩ መስፋቱን ተናግረዋል።

በተደረገው ማሻሻያና በተፈጠረው ሰፊ ምህዳርም በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው እየሰሩ ያሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ቁጥር 5 ሺህ 200 ደርሷል ብለዋል።

በመሆኑም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሁለንተናዊ የልማትና የማህበረሰብ አገልግሎት ተሳትፎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በቀጣይ በሚከበረው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሣምንት ድርጅቶች ስራዎቻቸውን ከማስተዋወቅ ባሻገር ጠንካራ የእርስ በርስ ትስስር የሚፈጥሩበት አጋጣሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version