አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በዩክሬን የሃይል መሰረተ ልማት ላይ ከባድ ፍንዳታዎች የተሰሙበት ጥቃት መፈጸሟን የሀገሪቱ ኢነርጂ ሚኒስትር ኽርማን ሃሉሼንኮ አስታውቀዋል፡፡
ከጥቃቱ ቀደም ብሎ የዩክሬን አየር ሃይል በመላው ሀገሪቱ የሚሳኤል ስጋት እንዳለ ማስጠንቀቂያ መስጠቱም ነው የተገለጸው፡፡
የቢቢሲ ዘገባ እንደሚለው፤ ሩሲያ በተደጋጋሚ የዩክሬን የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ጥቃት ፈጽማለች፡፡
በህዳር ወር ሀገሪቱ ሁለተኛ ጥቃት እንደተፈጸመባት የተገለጸ ሲሆን ፥ ጥቃቱን የፈፀሙት ድሮኖች በመላው ሀገሪቱ እየተዘዋወሩ እየበረሩ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡
ዩክሬን በዚህ ጥቃት የደረሰባትን ችግር ለመቀነስ የአደጋ ጊዜ አማራጯን እንደምትጠቀም ተነስቷል፡፡
በዚህ ወቅት ዩክሬን የአየር ሁኔታዋ እየቀዘቀዘና የመጀመሪያውን የበረዶ ዝናብ እያስተናገደች እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን፥ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከባዱ የቅዝቃዜና የበረዶ ዝናብን እንደምታስተናግድ ይገመታል፡፡
በዚህም ሩሲያ እንደ ቀድሞው ክረምት በዩክሬን የኃይል መሰረተ ልማቶቿ ላይ ጥቃት መፈጸሟን ከቀጠለች ሀገሪቱ ፈታኝ የሆኑ ወራትን እንደምታሳልፍ ተሰግቷል፡፡