የሀገር ውስጥ ዜና

የህብረቱን ከቀረጥ ነጻ የገበያ እድል በአግባቡ መጠቀም የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

By amele Demisew

November 28, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የሰጠውን ከቀረጥ ነፃ የገበያ እድል በአግባቡ መጠቀም የሚያስችል ውይይት ተካሂዷል፡፡

መድረኩ በአውሮፓ ህብረት የአካባቢን ዘላቂ ጠቀሜታ እውን ለማድረግ እየተተገበሩ ያሉ የሕግ ማዕቀፎች ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ አልባሳት በሚያመርቱ ኩባንያዎች ላይ የሚሳድረው ተጽዕኖ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የአውሮፓ ህብረት የአካባቢን ዘላቂ ጠቀሜታ እውን ለማድረግ እየተገበራቸው ያሉ የሕግ ማዕቀፎች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ተመርተው ወደ ህብረቱ ገበያ የሚቀርቡ አልባሳት ከአከባቢ ጋር ተስማሚ እንዲሆኑ እንደሚያስገድድ ተገልጿል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ፓርኮች ውስጥ ያሉ ባለሃብቶች ለዓለም ገበያ የሚያቀርቧቸው ምርቶች ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት የአልባሳት ውጤቶች መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

በውይይቱ የአውሮፓ ሕብረት ለኢትዮጵያ የሰጠውን ከኮታ እና ከቀረጥ ነጻ የገበያ እድል በአግባቡ መጠቀም ተገቢ ነው መባሉን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡