አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከማንቼስተር ዩናይትድ ምክትል አሰልጣኝነቱ በቅርቡ የለቀቀው ሩድ ቫን ኒስትሮይ የሌስተር ሲቲ አሰልጣኝ ለመሆን መስማማቱ ተገለፀ፡፡
ሆላንዳዊው አሰልጣኝ በውድድር ዓመቱ በሌስተር ሲቲ ቤት ደካማ አቋም ያሳዩትን ስቴቭ ኩፐርን በመተካት ነው በዋና አሰልጣኝነት ለመምራት የተስማማው፡፡
በስምምነቱ መሰረትም ቫን ኒስትሮይ ሌስተር በመጪው ቅዳሜ ከብረንትፎርድ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ቡድኑን በዋና አሰልጣኝነት ሊመራ እንደሚችል ተመላክቷል፡፡
አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካን በመተካት የሌስተር ሲቲ አሰልጣኝ የሆኑት ስቴቭ ኩፐር በስድስት ጨዋታዎች ተሸንፈው፣ በሁለቱ አሸንፈው በአራት ጨዋታ ደሞ አቻ ተለያይተዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት ሌስተር ሲቲ በቼልሲ 2 ለ 1 መሸነፉን ተክትሎም ሌስተር ሲቲ አሰልጣኝ ስቴቭ ኩፐርን ማስናበቱ ይታወሳል፡፡