Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሲዳማ ክልል በአራት ወራት ውስጥ ከ2 ሺህ 400 በላይ ቤቶች መሰራታቸው ተገለፀ

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል በአራት ወራት ውስጥ ከ2 ሺህ 400 በላይ ቤቶች ለአቅመ ደካሞች መሰራታቸው ተገለፀ፡፡

የ2016 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት መዝጊያና የ2017 የበጋ ወራት የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት መክፈቻ ስነ-ስርዓት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በተገኙበት በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ላኮ ከተማ ተካሂዷል።

አቶ ደስታ ሌዳሞ በዚህ ወቅት በሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት አማካኝነት ሁለት ለአቅመ ደካሞች የተሰሩ መኖሪያ ቤቶችን አስረክበዋል፡፡

ማህበራዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍላችን ድጋፍ ልናደርግ ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በአራት ወራት ውስጥ በክልሉ ከ2 ሺህ 400 በላይ ቤቶች በክልሉ መሰራቱን ተናግረዋል።

በክረምት በጎ አድራጎት የአረጋውያንና የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ፣ ለወላጅ አልባ ህፃናት የመማሪያ ቁሳቁስ ማበርከት፣ የአረንጓዴ አሻራ መርሐግር፣ ደም የመለገስና ሌሎች የበጎ አድራጎት ስራዎችን ሲከናወኑ መቆየታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version