Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሁን ያለው የሶማሊያ የፌዴራል መንግስት ሀገሪቱን ወደ ቀውስ እያመራት ነው- የሀገሪቱ የፓርላማ አባላት

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አሁን ያለው የሶማሊያ መንግስት አስተዳደር ሀገሪቷን ወደ ለየለት ቀውስ እየከተታት ነው ሲሉ የሀገሪቱ የፓርላማ አባላት ገለጹ፡፡

የፓርላማ አባላቱ ÷ የፌዴራል መንግስቱ የሀገሪቱን ህገ-መንግስት በመጣስ፣ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ወታደራዊ አፈናዎችን መጠቀም፣የጎሳ ልዩነትን በመፍጠር ግጭት መቀስቀስ፣ መንግሥታዊ ሙስናን በማስፋፋት እና በመሳሰሉት ህገ-ወጥ ድርጊቶች ሶማሊያን ወደ ለየለት ቀውስ እየማገዳት ነው ብለዋል፡፡

መንግስት ዜጎችን በማፈናቀል እና የሀገሪቱን ሀብት በመዝረፍ ለግል ጥቅም ማዋል ላይ ተጠምዷል ያሉት የፓርላማ አባላቱ÷ አሸባሪው አል ሸባብን ከመዋጋት ይልቅ የሀገሪቱ ጦር በጎሳ እንዲከፋፈል በማድረግ የሶማሊያ ሀገር መንግስት ህልውናን አደጋ ላይ ጥሏል ሲሉ ኮንነዋል፡፡

የፌዴራል መግስቱ የስልጣን ዘመኑን ያላግባብ ለማራዘም እየሰራ መሆኑን ገልጸው÷ ይህን አፍራሽ ድርጊቱን በአስቸኳይ እንዲያቆም አሳስበዋል፡፡

የፓርላማ አባላቱ አዲስ የጁባ ላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው ለተመረጡት አህመድ ሞሃመድ ኢስላም የእንኳን ደስአለዎት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Exit mobile version