የሀገር ውስጥ ዜና

66 መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By ዮሐንስ ደርበው

November 27, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 66 መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞች በሁለት ዙር በረራ ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ መደረጉን በጅቡቲ የኢትዮያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

ስደተኞቹ  ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የተደረገው ኤምባሲው ጅቡቲ ከሚገኘው ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሕገ-ወጥ መንገድ ከሀገር መውጣት ለሰውም ሆነ ለሀገር ጉዳት የሚያስከትል በመሆኑ ከዚህ ተግባር መቆጠብ እንደሚገባም ኤምባሲው አሳስቧል፡፡