Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር እና ብሔራዊ ባንክ በጋራ በሚሠሩባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፋይናንስ ሥነ-ምኅዳሩን አካታችና ምቹ ለማድረግ በቅንጅት መስራት በሚያስችሉ ጉዳች ላይ ከብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምኅረቱ ጋር መምከራቸውን የሥራ እና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ፡፡

ሚኒስትሯ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የፋይናንስ ተቋማት በክኅሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና በሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት ውስጥ የጎላ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

በዚህም የፋይናንስ ሥነ-ምኅዳሩን አካታች፣ ፈጠራ የታከለበት እና ምቹ በማድረግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማላቅ የሚያስችሉ ሥራዎችን ቀጣይነት ባለው መልኩ በቅንጅት ለመስራት ከመግባባት መደረሱን ተናግረዋል፡፡

የባንኩ ገዥም የፋይናንስ ሥነ-ምኅዳሩን አካታችና ለዘርፉ ሥራዎች ምቹ ለማድረግ ብሎም በቅንጅት ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠውልኛል ብለዋል፡፡

Exit mobile version